የኢትዮጲያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር ከሚሰራባቸው ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ቅርስን የመጠበቅ የመንከባከብና ለመጪው ትውልድ የማስተላለፍ ተግባራት ውስጥ አንዱ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ጉዳት የደረሰባቸውን ቅርሶች ታሪካዊነታቸው እንደተጠበቀ ማደስ ነው፡፡በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው እና እ.ኤ.አ በ1890 የተገነባው የራስ ከበደ መንገሻ መኖሪያ የነበረው ቅርስ ቤት እድሳት ታሪካዊነቱ እንደተጠበቀ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር አማካኝነት በመታደስ ላይ ይገኛል፡፡በአሁኑ ወቅት የቅርስ ቤቱ የማሕበሩ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ በመሆን እያገለገለ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር
ቅርስ ያለው ታሪክ አለው!
26/12/2017ዓ.ም





Leave a Reply