የአዋሽ ባንክ እና የአዋሽ ኢንሹራንስ የማኔጅመንት አባላት እና ሠራተኞች 20,000 ሐገር በቀል ችግኞችን በእንጦጦ የተፈጥሮ ፓርክ ተከሉ፡፡

—

by

እህት ኩባንያዎቹ ችግኝ በመትከል ተፈጥሮን እንንከባከብ በሚል መሪ ቃል ከ 2000 በላይ ሠራተኞችን ባሳተፈ መልኩ የችግኝ ተከላ መርሀግብር በዛሬው ዕለት ሐምሌ 13/2017 ከኢትዮዽያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር ጋር በመተባበር አካሂደዋል። መንትያ ተቋማቱ ላለፉት 6 ዓመታት ችግኞችን የመትከል እና የመንከባከብ ስራን ከፍተኛ በጀት በመመደብ ሲሰሩ ቆይተዋል።አቶ ፀሀይ ሽፈራው የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና አቶ ጅባት አለምነህ የአዋሽ ኢንሹራንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ በጋራ ባስተላለፉት መልዕክት እህት ኩባንያዎቹ በዛሬው ዕለት የሚተከሉትን 20,000 ችግኞች በቀጣይ ደን እስከሚሆኑ ድረስ በጀት በመመደብና ክትትል በማድረግ ቀጣይነት ያለው ስራ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።አክለውም አዋሽ ለየትኛውም ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የማሕበራችንን አላማ በመረዳት በጋራ ለሚሠራው አጋራችን አዋሽ(አዋሽ ባንክ እና አዋሽ ኢንሹራንስ) ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር
አዲስ አበባ
ቅርስ ያለው ታሪክ አለው!
13/11/2017ዓ.ም


Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *