የባንኩ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት እና ሠራተኞች ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበር ጋር በመተባበር በዛሬው ዕለት 2000 የሐገር በቀል ችግኞችን በእንጦጦ የተፈጥሮ ፓርክ ተክለዋል።በዕለቱም የማሕበሩ ቦርድ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፀደቀ አባተ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገው ተፈጥሮን በመጠበቅ የአየር ንብረትን መጠበቅ እና ለቀጣይ ትውልድ ይህን በጎ ተግባር ማስተላለፍ እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።ዳሽን ባንክ ላለፉት 5 ዓመታት የሐገር በቀል ችግኞችን የመትከል እና የመንከባከብ ስራን ከፍተኛ በጀት በመመደብና ትኩረት በመስጠት በእንጦጦ የተፈጥሮ ፓርክ ሲሰራ ቆይቷል።የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው አለሙ የዳሽን ባንክ አንዱ አላማ ለህብረተሰቡ መልሶ መስጠትና ማህበረሰቡ ውስጥ መስራት ነው ሲሉ ገልፀዋል።አያይዘውም ባንኩ ከማሕበሩ ጋር እየሰራ ያለውን ተፈጥሮን የመንከባከብ ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የማሕበራችንን አላማ በመረዳት በጋራ ለሚሠራው አጋራችን ዳሽን ባንክ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማሕበርአዲስ አበባቅርስ ያለው ታሪክ አለው! 12/11/2017 ዓ.ም









Leave a Reply